ከሳዑዲ ዓረቢያ 1 ሺህ 106 ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

By Shambel Mihret

December 22, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 106 ዜጎች በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ሒደት ተጠናክሮ መቀጠሉንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡