ኖርዌይ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኖርዌይ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍና የመልሶ መቋቋም ሂደት አጠናክራ እንደምትቀጥል በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር እና በአፍሪካ ሕብረት የኖርዌይ ቋሚ ተወካይ አምባሳደር ስቲያን ክሪስቴንሰን ተናገሩ፡፡
አምባሳደር ስቲያን ክሪስቴንሰን ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ነገዎ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱ ላይ አምባሳደር ስቲያን ክሪስቴንሰን እንደገለጹት÷ ኖርዌይ በኢትዮጵያ የሰሜኑ ክፍልና በሌሎች አካባቢዎች በተፈጠረው ግጭት ምክንያት የተጎዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን እና መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት ድጋፏን አጠናክራ ትቀጥላለች፡፡
መንግስት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት የኖርዌይ መንግስት ያበረታታል ማለታቸውን የሕዝብ ተወካዮች መረጃ ያመላክታል፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ነገዎበበኩላቸው÷ በግጭቱ ወቅት የተጎዱ ዜጎችን መልሶ በማቋቋም እና የወደሙ መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ሂደት የአጋር ሀገራት ሚና ከፍኛ ሚና አለው ብለዋል፡፡