የሀገር ውስጥ ዜና

በቤተሰብ ዕቅድና ጤና አጠባበቅ ላይ የሚተገበር 2 ሚሊየን ዶላር የሚጠጋ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

By Tamrat Bishaw

December 23, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በቤተሰብ ዕቅድና ጤና አጠባበቅ ላይ የሚተገበር የ 1 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ፡፡

ፕሮጀክቱ በሦስት ዓመት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ እና በኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር እንዲሁም በፓካርድ ፋውንዴሽን አማካኝነት ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡

1ነጥብ 4 ሚልየን ዶላሩ ለቤተሰብ ዕቅድ ማስፋፋትና ጤና ጥራት አጠባበቅ እንዲሁም ግማሽ ሚሊየን ያህሉ በሀገሪቱ በፀጥታ ችግር ምክንያት የጤና ሥርዓታቸው ለተዛባባቸው አካባቢዎች እገዛ ይውላል፡፡

ፕሮጀክቱ በርካታ እናቶች የቤተሰብ ዕቅድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ታምኖበታል፡፡

በዘቢብ ተክላይ