የሀገር ውስጥ ዜና

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የብዝኃ ቋንቋ ሥርዓተ ትምህርትን ለመወሰን በተደረገው ጥናት ላይ ተወያየ

By Amele Demsew

December 23, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው 8ኛ መደበኛ ስብሰባ ከሐምሌ 2014 ጀምሮ በኮተቤ የትምህርት ዩንቨርሲቲ ሲጠና በቆየው የብዝኃ ቋንቋ ሥርዓተ ትምህርትን ለመወሰን በተደረገው ጥናት ላይ ዝርዝር ውይይት አድርጓል። ለቀጣይም ከዘርፉ ባለሙያዎች፣ ከባለድርሻ እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ተደርጎበት እና ተጨማሪ ግብዓት ተወስዶበት የብዝኃ ቋንቋ ሥርዓተ ትምህርቱ ለውሳኔ እንዲቀርብ አቅጣጫ መሰጠቱን የከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።