የኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማህበር “ኦንላይን” ድጋፍ ማሰባሰብ የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ
አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማህበር “ኦንላይን” ድጋፍ ማሰባሰብ የሚያስችለውን ስምምነት ቻፓ ፋይናንሺያል ቴክኖሎጅ ከተሰኘ ድርጅት ጋር ተፈራርሟል።
ስምምነቱ በጦርነትና በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ድጋፍ ለማድረግ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን “ኦንላይን” በሚሰሩ የተለያዩ አማራጮች እንዲጠቀሙ የሚያስችል መሆኑን የማህበሩ የሀብት ማሰባሰብና ማስፋፋት አገልግሎት መምሪያ ሀላፊ አህመድ ይማም ተናግረዋል።
የ”ኦንላይን” ድጋፍ ማድረግ የሚፈልጉ ሰዎች በማስተር ካርድ፣ ቪዛ ካርድ፣ ፔይፓል፣ በሞባይል ባንኪንግ ፣ ቴሌብር እንዲሁም ኪው አር ኮድ አማካኝነት መለገስ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
የ”ኦንላይን” መለገሻው ከዛሬ ጀምሮ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተመላክቷል፡፡
በቅድስት አባተ