የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል ከ810 ሺህ ሄክታር በላይ በመስኖ ስንዴ ተሸፍኗል – አቶ ሽመልስ አብዲሳ

By Tamrat Bishaw

December 23, 2022

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 14 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ከ810 ሺህ ሄክታር በላይ በመስኖ ስንዴ መሸፈኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ አስታወቁ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ “የግብርና ትራንስፎርሜሽን የወደፊቱ መንገዳችን ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

“አርሶ አደሮቻችን እውነተኛ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን በተግባር አሳይተዋል” ብለዋል በጽሁፋቸው።

ርዕሰ መስተዳድሩ የወደፊቱን በተግባር እየገነባን ነው ሲሉም መልዕክታቸውን አስፍረዋል።