Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐዋሳ ከተማ የተገነባውን ዳቦ ፋብሪካ መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐዋሳ ከተማ የተገነባውን ዳቦ ፋብሪካ መርቀው ከፈቱ።

የዳቦ ፋብሪካው በቀን 300 ሺህ ዳቦ እና 42 ቶን ዱቄት የማምረት አቅም እንዳለው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ፋብሪካው በቀዳማዊት እመቤት ፅህፈት ቤት አማካኝነት በመላ ሃገሪቱ ከሚገነቡት 11 የዳቦ ፋብሪካዎች አራተኛው መሆኑንም ነው ያስታወቁት።

ፋብሪካው ለአካባቢው ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ዳቦ እንደሚያቀርብም ጠቅሰዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.