Fana: At a Speed of Life!

የአሜሪካው ኤግዚም ባንክ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የ281 ሚሊየን ዶላር የብድር መተማመኛ አፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ኤግዚም (ኢምፖርት ኤክስፖርት) ባንክ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ የ281 ሚሊየን ዶላር የብድር መተማመኛ አፀደቀ።

ባንኩ ያፀደቀው የብድር መተማመኛ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖችን ለመግዛት እንደሚውል ተገልጿል።

ከዚህ ባለፈም በአሜሪካ የተለያዩ አካባቢዎች ለ1 ሺህ 600 ሰዎች የሥራ እድል ለመፍጠር እንደሚያግዝ የባንኩ መረጃ ያመላክታል።

ባንኩ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በተጨማሪም ለዩናይትድ ኪንግደም 407 ሚሊየን ዶላር የብድር መተማመኛ ማፅደቁንም አስታውቋል።

በአጠቃላይ ባንኩ 688 ሚሊየን ዶላር የብድር መተማመኛን ያፀደቀ ሲሆን፥ ይህም በአሜሪካ ለ4 ሺህ ዜጎች የስራ እድል ለመፍጠር እንደሚያግዝም ገልጿል።

ውሳኔው ባንኩ ከሀገራቱ ጋር ያለውን ትስስር የሚያጎለብት መሆኑንም ነው የገለጸው።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.