Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ በክረምቱ ቅዝቃዜ ማየል ምክንያት እስካሁን የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ በክረምት ቅዝቃዜ ሳቢያ እስካሁን 12 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተገለፀ።

በበረዶ ግግር ምክንያት እንቅስቃሴዎች መስተጓጎላቸውን ነው መረጃዎች ያመላክቱት።

በአንዳንድ አካባቢዎችም ቅዝቃዜው ከዜሮ በታች እስከ ነጌቲቭ 45 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ መድረሱን የአየር ሁኔታ መረጃዎችን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የክረምቱ የበረዶ ውሽንፍርና ማዕበል ጋር ተያይዞም 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ሰዎች የኃይል አቅርቦት እንደተቋረጠባቸው ተገልጿል፡፡

የበረዶ ውሽንፍርና ማዕበሉ 200 ሚሊየን አሜሪካውያን ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ተፅዕኖ ማሳረፉንም ነው ዘገባው ያመላከተው።

የበረዶ ማዕበሉ ከአሜሪካዋ ቴክሳስ ግዛት እስከ ካናዳ ኪዩቤክ 3 ሺህ 200 ኪሎ ሜትር ሸፍኗል ነው የተባለው።

በርካታ የአሜሪካ ግዛቶች አሁን ላይ “ፍጹም ቀዝቃዛ” በሚባል የአየር ንብረት ውስጥ ሲሆኑ፥ አንዳንድ አካባቢዎችም የክረምት ማዕበል ማስጠንቀቂያ ውስጥ መግባታቸውም ነው የተነገረው።

በፔንሲልቫኒያ፣ ሚቺጋን እና ኒውዮርክም ከባድ የበረዶ ግግር ስጋት የተደቀነ ሲሆን፥ ከ8 ሚሊየን በላይ ነዋሪዎች በስጋት ውስጥ ናቸው ተብሏል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.