Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ለሥራ ዕድል ፈጠራ የተሰራጨ ከ300 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ አልተሰበሰበም

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በገጠርና በከተማ ለሥራ ዕድል የተሰራጨ ከ300 ሚሊየን ብር በላይ አለመመለሱን የክልሉ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ቢሮው በ2015 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት አፈፃፀም ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቴፒ ከተማ ውይይት አድርጓል፡፡

የቢሮው ምክትል ኃላፊና የገጠር ሥራ ዕድል ዘርፍ ኃላፊ ሰሎሞን አየለ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት÷ ያልተመለሰው ብድር በገጠር ከ2005 ዓ.ም በከተማ ደግሞ ከ2009 ጀምሮ ለወጣቶች የተሰራጨ ብድር ነው፡፡

በፌደራል፣ በክልል፣ በዞን፣ በወረዳ እንዲሁም በከተማ አስተዳደር አማካኝነት በክልሉ ከ2005 ዓ.ም ጀምሮ ከ539 ሚሊየን ብር በላይ ገንዘብ በብድር መሰራጨቱን እና ከዚህ ውስጥ እስከ 2014 ዓ.ም የተመለሰው ገንዘብ 289 ሚሊየን ብር ገደማ ነው ብለዋል፡፡

ከ300 ሚሊየን ብር በላይ ውዝፍ ብድር አለመመለሱ በክልሉ የተለዩ ከ98ሺህ በላይ ወጣቶችን በሥራ ማሰማራት እንዳይቻል እንቅፋት ሆኗል ነው ያሉት፡፡

ብድር የማስመለስ ሥራውን በባለቤትነት መምራት አለመቻል፣ ለጉዳዩ ትኩረት አለመስጠት፣ የተጠያቂነት ሥርዓቱ የላላ መሆንና ሌሎችም ችግሮች የተሰራጨው ብድር እንዳይመለስ ያደረጉ ምክንያቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

በተስፋየ ምሬሳ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.