Fana: At a Speed of Life!

ለኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ቁሶች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገቢዎች ሚኒስቴር እና ጉሙሩክ ኮሚሽን ለኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸውን ቁሶች ድጋፍ አደረጉ፡፡

ድጋፉ በዞኑ በሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ማቋቋሚያ የሚውል ሲሆን÷ አልባሳትና ምግብ ነክ ቁሶችን ያከተተ ነው፡፡

ድጋፉን የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሤ እና የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በከሚሴ ከተማ ተገኝተው አስረክበዋል።

ወይዘሮ ዓይናለም ንጉሤ በድጋፍ እርክክቡ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በተቋማት የሚደረጉ ድጋፎች ችግሮችን በጊዜያዊነት ለማለፍ እንደሚረዱ ጠቁመው ዞኑ የሚያጋጥሙትን ችግሮች በዘላቂነት ለመቅረፍ ያለውን እምቅ አቅም በአግባቡ መጠቀም ይገባዋል ብለዋል፡፡

አቶ ደበሌ ቃበታ እንደገለጹት÷ ከለውጡ በኋላ ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ከስምንት ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጡ ቁሶችን ኮሚሽኑ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉን የተረከቡት የከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድጃ አሊ÷ ድጋፉ በጦርነት እና በሌሎች ተፈጥሯዊ አደጋዎች ጉዳት ለደረሰባቸው አካላት በትክክል እና በወቅቱ ይደርሳል ማለታቸውን የጉሙሩክ ኮሚሽን መረጀ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.