Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል የወተት፣የዶሮ፣የስጋና የማር ምርት ማሻሻያ ማስተዋወቂያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የወተት፣የዶሮ፣የስጋና የማር ምርት ማሻሻያ ማስተዋወቂያ መርሐ ግብር በጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ እየተካሄደ ነው፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ይፋ የተደረገው የ ’ሌማት ትሩፋት’ መርሐ-ግብር በምግብ ሉዓላዊነትን ማስከበር እና ክብርን ከማረጋገጥ ጋር ቁርኝት አለው ተብሏል ።

በመድረኩ የ ’ሌማት ትሩፋት’ መርሐ-ግብር ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትዋናን እንድታረጋግጥ ማስቻል፤ በተለይም ስጋ፣ እንቁላል፣ ማር እና ወተት ቅንጦት ሳይሆን ትርፍ ምርት ሆነው እንዲገኙ ማድረግን ታሳቢ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል ።

በመርሐ ግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ ፣የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው እንዲሁም የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

በምንተስኖት ሙሉጌታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.