Fana: At a Speed of Life!

መዲናችን የሁላችን እንደመሆኗ ለእድገቷ ሁሉም የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊያበረክት ይገባል -ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)መዲናችን የጋራችንና የሁላችን እንደመሆኗ መጠን ሁሉም ሀላፊነት የሚሰማው ዜጋ ስለ እድገቷና ቀጣይ ስራዎች በሀሳብ ፣በጉልበት እና በገንዘብም የየድርሻውን ሊያበረክት ይገባል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

ከንቲባዋ ከመዲናዋ ምሁራን ፣ የሚዲያ ባለሙያዎች ፣ የእምነት አባቶች ፣ ታዋቂ ሰዎችና የማህበረሰብ አንቂዎች ጋር በከተማ አስተዳደሩ የ15 ወራት የእቅድ አፈፃፀምና ቀጣይ እቅዶች እንዲሁም ወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

አዲስ አበባን በመመካከር፣ በመተባበር፣ በመደማመጥ እና በሰለጠነ የሀሳብ ልዕልና ሰላማዊ ለነዋሪዎቿ ምቹ እንደ ስሟ አበባ ማድረጋችንን እንቀጥላለንም ነው ያሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.