ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በሰላም ሂደቱ አፈጻጸም እና ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት በሰላም ሂደቱ አፈጻጸም እና ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ÷ በፕሪቶሪያ በተደረሰው የሰላም ስምምነት አፈጻጸም ላይ እና እሱን ተከትሎ ሁለት ጊዜ በናይሮቢ በነበሩ ውይይቶች አተገባበር ላይ ምክክር ተደርጓል ።
የሰላም ሂደቱ እስካሁን ከነበረው በተሻለ አፈጻጸም እንዲሄድ መንግስት ልክ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ አስፈላጊውን እንደሚያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገልጸዋል ።
በአልዓዛር ታደለ