Fana: At a Speed of Life!

በመላው ዓለም ኢትዮጵያን የወከሉ ዲፕሎማቶች ሀገር የተጋፈጠቻቸውን ፈተናዎች እንድትሻገር ላስመዘገቡት ስኬት ምስጋና ይገባቸዋል- አቶ ደመቀ መኮንን

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 17፣ 2015 ( ኤፍ ቢ ሲ) በመላው ዓለም ኢትዮጵያን የወከሉ ዲፕሎማቶች ባለፉት ሁለት አመታት ሀገር የተጋፈጠቻቸውን ፈተናዎች እንድትሻገር በጋራ ዘመቻ ላስመዘገቡት ስኬት ምስጋና ይገባቸዋል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች ፣አምባሳደሮች እና ምክትል የሚሲዮን መሪዎች ዓመታዊ ስብሰባና ስልጠና ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።

በመድረኩ ጅማሮ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት አቶ ደመቀ መኮንን በዓለም አቀፍ መድረክ የኢትዮጵያን ተሳትፎ ማሳደግና ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ የተያዘውን ትኩረት ለማሳካት በዘመቻ የተሰራው ስራ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል የተመዘገበበት ነው ብለዋል።

በቀጣይም አዳዲስ ጫናዎችና አጀንዳዎች መምጣታቸው ስለማይቀር ቀሪ የዲፕሎማሲ የቤት ስራዎችን ታሳቢ ያደረገ የላቀ ሀላፊነት እንዳለብን ሊታወቅ ይገባልም ነው ያሉት።

ዛሬ የጀመረው የከፍተኛ አመራሮች፣ አምባሳደሮች፣ ምክትል የሚሲዮን መሪዎች ስብሰባና ስልጠና÷ ያለፈው ዲፕሎማሲያዊ ስራ የእቅድ አፈጻጸም ግምገማና ቀጣይ የዲፕሎማሲ ስራ ትኩረቶች እቅድ ምልከታ የሚደረግበት ይሆናል።

በበርናባስ ተስፋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.