Fana: At a Speed of Life!

ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል ጃፓን ገለጸች

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 17 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጃፓን ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል በኢትዮጵያ የሀገሪቱ አምባሳደር ኢቶ ታካኮ ገለጹ።

የጃፓን መንግሥት ለሀገራዊ ምክክሩ ሥራ የሚውሉ ከ7 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸውን ሁለት ተሽከርካሪዎች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኩል ድጋፍ አድርጋለች።

መንግሥታቸው ለኢትዮጵያ ዘላቂ ልማት የሚረዱ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ በማድረግ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በሀገራዊ ምክክሩ ሁሉንም የኅብረተሰብ ክፍል በማሳተፍ ብሔራዊ መግባባትና ዘላቂ ሠላም ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት ጃፓን እንደምትደግፍ ገልጸዋል።

ይህንን ተከትሎ ጃፓን ለኮሚሽኑና በምክክር መድረኩ ለሚሳተፉ የኅብረተሰብ ክፍሎች መገልገያ የሚውል ሁለት ተሽከርካሪዎችን ድጋፍ ማድረጓን ኢዜአ ዘግቧል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጣሰው ወልደሃና በበኩላቸው፥ የጃፓን መንግሥት ለኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋና በማቅረብ ለሀገራዊ ምክክሩ ያደረገችው ድጋፍም ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው መሆኑን አንስተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.