Fana: At a Speed of Life!

አሉታዊ መጤ ባህሎች እና ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተገለፀ

 

አዲሰ አበባ፣ ታኅሣሥ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች እና አሉታዊ መጤ ባህሎችን በመከላከል፣ የስራና ቁጠባ ባህልን በማሳደግ ብዝሃ ባህልን ለማጎልበትና ማህበራዊ ትስስርን በማጠናከር ዙሪያ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ በሐረር ከተማ ተጀምሯል።

በዚህ ወቅት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የባህልና ቋንቋ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ወርቅነሽ ብሩ፥ ጎጂ ልምምዶችን መቀነስና ድርጊቱን መዋጋት እንደሚገባ ገልፀው ለዚህም በቅንጅት መንቀሳቀሱ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

ለአንድ ወር የሚቆየውና “የባህል ፀጋዎቻችንን በማጎልበት ትውልድን እንገባ” በሚል መሪ ቃል የተጀመረው ንቅናቄ በተለይም ግንዛቤን ከማሳደግ አንፃር ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡

የሐረሪ ክልል ባህል ቅርስና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ተወለዳ አብዶሽ በበኩላቸው፥ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና አስተሳሰቦች በአኩሪ ኢትዮጵያዊ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያስከተሉና ከፍተኛ የማህበራዊ፣ ኢኮኖማያዊና ስነልቦናዊ ቀውስ እያደረሱ መሆኑን ጠቁመዋል።

በመሆኑም ችግሩ የከፋ ደረጃ ከመድረሱ በፊት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የሀይማኖት ተቋማት ሌሎች አካላት በተለይም ህብረተሰቡ በትኩረት ሊሰሩበት እንደሚገባ መናገራቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.