1 ሺህ 187 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 187 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ከተመላሾቹ ውስጥም 358ቱ ሴቶች ሲሆኑ÷ 57 የሚሆኑት ደግሞ ህጻናትና ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ለተመላሽ ዜጎች በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
ከህዳር 12 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን በተከናወነ ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራም በአጠቃላይ 18 ሺህ 280 ኢትዮጵያውያንን መመለስ መቻሉ ተጠቁሟል፡፡