ውሎና አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ 21 ሺህ የሚጠጉ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ውሎና አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ 20 ሺህ 991 ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
በ11 ከተሞች በተተገበረ 1ኛ ዙር የልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮጀክት ውሎና አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ 20 ሺህ 991 ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ መረጃ ያመላክታል፡፡
ሚኒስቴሩ በፕሮጀክቱ ትግበራና አፈጻጸም ላይ የተከናወኑ ሥራዎችን አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ በሰጡት መግለጫ፥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር እና ከአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ጋር ውል በመግባት ውሎና አዳራቸውን ጎዳና ላይ ያደረጉ ሕጻናት፣ አዋቂዎች፣ ሕጻናትን የያዙ እናቶች እና አረጋውያን ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች ለችግር ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በዘላቂነት ለመደገፍና ለማቋቋም እንዲያስችል የተቀረፀው የማኅበራዊ ጥበቃ ፈንድ ፀድቆ በሥራ ላይ እንዲውል ጥረት ይደረጋል ማለታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ይጠቁማል፡፡
የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ አየለች እሸቴ እንደገለጹት÷ ሚኒስቴሩ ሀብት የማሰባሰብ፣ ሥራዎችን የማስተባበር፣ የድጋፍና ክትትል ተግባራትን የማከናወን፣ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን የማመቻቸት የፕሮጀክት ዕቅድ አዘጋጅቶ በቅንጅት ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡
ዜጎች ወደ ጎዳና እንዳይወጡ በማህበረሰብ አቀፍ ጥምረት የሚደገፉበትን አሠራር ከመዘርጋት ባለፈ ከወጡ በኋላ ተገቢውን የተሃድሶ፣ የምክር፣ የስልጠናና መሰል አገልግሎቶችን አግኝተው ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ እየተሠራ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!