ለጋምቤላ ክልል የ36 ዘመናዊ ትራክተሮችና 150 የውሃ መሳቢያ ጀነሬተሮች ድጋፍ ተደረገ
የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሀመድ÷ ክልሉ ሰፊ መሬትና ውሃ የታደለ እንደመሆኑ የግብርና ሜካናይዜሽን ግብዓቶቹ መሬቱን ከውሃ ጋር በማገናኘት አደጋ የመቋቋም አቅምን ለማሳደግ ብሎም ምርታማነትን ለማምጣት ትልቅ እገዛ ያደርጋል ብለዋል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በበኩላቸው ÷ ለተደረገው ድጋፍ አመስግነው ድጋፉ ክልሉ በግብርና ዘርፍ የጀመረውን ተግባር የሚያግዝና ከአርሶ አደሩና አርብቶ አደሩ እየቀረበ ያለውን የሜካናይዜሽን ግብዓት አቅርቦት ጥያቄ የሚመልስ ነው ማለታውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡