በሰሜኑ አካባቢ የተፈጠረውን ግጭት በሰላም ለመፍታት የተጀመረው እንቅስቃሴ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ተሸጋግሯል – አቶ ደመቀ መኮንን
አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሀገራችን በሰሜኑ አካባቢ የተፈጠረውን ግጭት በሰላም ለመፍታት የተጀመረው እንቅስቃሴ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ተሸጋግሯል አሉ፡፡
አቶ ደመቀ መኮንን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ የጠንካራ ዲፕሎማሲ ስራ መሠረቱ ጠንካራ ውስጣዊ ሁኔታ መሆኑን አስታውቀዋል።
እየተካሄደ ባለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የከፍተኛ አመራሮች እና የሚሽን መሪዎች ውይይት ላይ ይህ ጉዳይ በአጽንኦት መነሳቱን ጠቁመዋል።
በሰሜኑ አካባቢ የተፈጠረውን ግጭት በሰላም ለመፍታት የተጀመረው እንቅስቃሴ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩን ጠቅሰው፥ በሌሎች አካባቢዎች ያለውን የሰላም ሁኔታ ለማሻሻል እና የዜጎችን ሰላም እና ደኅንነት እንዲሁም ተጠያቂነት የማረጋገጡ ጉዳይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
ዲፕሎማሲያችን በሀገር ውስጥ የተፈጠረውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀምና በውጭ የተጀመረውን መልካም ግንኙነት የበለጠ በማፅናት ብሔራዊ ጥቅማችንን የማስጠበቅና ተደማጭነታችንን የማሳደግ ተልዕኮ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታልም ነው ያሉት።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!