Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የተጀመረው የሰላም ሂደት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የሚፈለገው ውጤት እንዲመጣ የሕዝቡ አጋርነት ሰፊ ሚና እንዳለው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል የተጀመረው የሰላም ሂደት ተጠናክሮ እንዲቀጥልና የሚፈለገው ውጤት እንዲመጣ የሕዝቡ አጋርነት ሰፊ ሚና እንዳለው በአድዋ ከተማ በተደረገው ሕዝባዊ የምክክር መድረክ ተገለጸ።

በመድረኩ የፌደራል መንግስት ከሰላም ሰምምነቱ በኋላ በክልሉ ሰላምን ለማምጣት እና መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት እያደረገ ያለው ጥረት እንዲሁም በሰብዓዊ አቅርቦት ላይ  እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ቀርበዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎችም እስካሁን የተሰራውን ስራ አድንቀው ለቀጣይም ብሩህ ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።

ሰብዓዊ አቅርቦትን በተመለከተም የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በአድዋ እና አካባቢው ያለውን ሰላም ለማጠናከር በፌደራል መንግስት በኩል እየተሰራ ያለው ተግባር ሊጠናከር እና ሊሰፋ እንደሚገባም ነው የገለጹት፡፡

በአድዋ እና አካባቢውም ሆነ በትግራይ ክልል ያለው ሰላም ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚችለው የሕዝብ አጋርነት ሲኖር መሆኑ በመድረኩ ተነስቷል።

በለይኩን ዓለም፣ አፈወርቅ እያዩ እና ታሪኩ ወልደሰንበት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.