Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ከ1 ነጥብ 9 ትሪሊየን ብር በላይ የገንዘብ ልውውጥ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ከ1 ነጥብ 9 ትሪሊየን ብር በላይ የገንዘብ ልውውጥ ማድረጉን አስታወቀ፡፡

ባንኩ ባለፉት 12 ወራት ነው በዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ብቻ ከ1 ነጥብ 9 ትሪሊየን ብር በላይ የገንዘብ ልውውጥ ያደረገው፡፡

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ÷ የገንዘብ ልውውጡን ማድረግ የተቻለው በሞባይል ባንኪንግ፣ ሲቢኢ ብር፣ ኢንተርኔት ባንኪንግ፣ ኤቲኤም እና በፖስ የባንኩ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች መሆኑን መግለፃቸውን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.