የሀገር ውስጥ ዜና

በአዳማ ከተማ በደረሰ ፍንዳታ የአንድ ሰው ህይወት አለፈ

By Mekoya Hailemariam

December 27, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ደደቻ አራራ ቀበሌ ጉዲሳ በተባለው ሆቴል በተከሰተዉ ፍንዳታ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን አስታወቀ፡፡

በአደጋው በሶስት ሰዎች ላይ የመቁሰል አደጋ መድረሱም ተመላክቷል፡፡

ፈንዳታውን አድርሰዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ በሆቴሉ አካበቢ ያለው ማህበረሰብ ለመርማሪ ፖሊሶች አስፈላጊውን መረጃ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡