Fana: At a Speed of Life!

ከ57 ሺህ 295 በላይ ሜትሪክ ቶን ኤን.ፒ.ኤስ የአፈር ማዳበሪያ ጅቡቲ ተራገፈ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ2015/16 የምርት ዘመን ወደ ሀገር ውስጥ ከሚገባው የአፈር ማዳበሪያ የመጀመሪያውን ከ57 ሺህ 295 ሜትሪክ ቶን ኤን. ፒ.ኤስ ማዳበሪያ ጅቡቲ ተራግፏል፡፡

ከሞሮኮ የአፈር ማዳበሪያ የጫነች የመጀመሪያዋ መርከብ ትናንት ጅቡቲ ማራገፏን የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት መረጃ ያመላክታል፡፡

በሦስተኛው የኦፕሬሽን ሽፍት /በምሽት ሽፍት/ ከ2 ሺህ 370 ሜትሪክ ቶን በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ ሀገር ውስጥ ማስገባት መቻሉም ነው የተገለጸው፡፡

ኢባትሎአድ የማጓጓዝ ሥራውን በበቂ ዝግጅት በመጀመሩ መርከብ ወደብ በደረሰ በሰዓታት ውስጥ ወደ ሀገር ውስጥ የመጫንና የማጓጓዝ ሥራ በፍጥነት ማከናወን እንዳስቻለው ተመላክቷል፡፡

በቀጣይ 15 ቀናት ውስጥ እያንዳንዳቸው 60 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ የጫኑ ሁለት ግዙፍ መርከቦች ጅቡቲ እንደሚደርሱ ይጠበቃል፡፡

የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ላለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት ከፍተኛ መጠን ያለው የአፈር ማዳበሪያን በታቀደለት ጊዜ አጓጉዞ በስኬት ማጠናቀቁ እና ይህ ለአራተኛ ጊዜ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.