Fana: At a Speed of Life!

በገናና ጥምቀት በዓላት ላይ የምርት እጥረት እንዳይፈጠር ቁጥጥር የሚያደርግ ግብረ ኃይል ወደ ሥራ ገባ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በገናና ጥምቀት በዓላት ላይ የምርት እጥረት እንዳይፈጠር ቁጥጥርና ክትትል የሚያደርግ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዳነ ሱሌ እንደገለጹት÷ የምርት አቅርቦት እና ፍላጎት አለመጣጣም እንዳይከሰት ከበዓላቱ በፊት በልዩ ትኩረት መሥራት አስፈላጊ በመሆኑ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡

የሚመለከታቸው አካላትም ከወዲሁ ምርቶቹን እንዲያከፋፍሉ በተመደቡባቸው ቦታዎች እንዲያስገቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ከምርት አቅርቦቱ ጎን ለጎን÷ የጥራት፣ የዋጋ፣ የመጠን እንዲሁም ሕጋዊነት ክትትልና ቁጥጥር ተግባራት ይሠራል ማለታቸውንም የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

በዓላቱን ታሳቢ በማድረግ ለሸማቹ ሕብረተሰብ የሚቀርቡ የድጎማ ፣ የግብርናና ኢንዱስትሪ ምርቶች አቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር ቁጥጥር መደረግ እንዳለበት ተጠቁሟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.