መቀሌን ጨምሮ 27 ከተሞች ዳግም የቴሌኮም አገልግሎት አገኙ
አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሪጅን መቀሌን ጨምሮ 27 ከተሞች ዳግም የቴሌኮም አገልግሎት አገኙ።
ዋና ስራ አስፈጻሚዋ በጦርነት ምክንያት ጉዳት የደረሰበት የሰሜን ሪጅን 981 ኪሎ ሜትር የፋይበር ጥገና በኢትዮ ቴሌኮም መከናወኑንም አስረድተዋል።
በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የስልክ አገልግሎትም በዛሬው ዕለት መቀሌ ላይ የተሳካ ጥሪ ማድረግ መቻሉንም ነው የተናገሩት።
የቴሌኮም አገልግሎቱ ዳግም መጀመሩን ተከትሎም 61 የባንክ ቅርንጫፎች ወደ ስራ ገብተዋል ነው ያሉት።
በምንይችል አዘዘው