Fana: At a Speed of Life!

አየር መንገዱ ከፊታችን አርብ ጀምሮ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን በረራ በቀን ወደ 2 ጊዜ አሳደገ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከፊታችን አርብ ታኅሣሥ 21 ቀን 2015 ጀምሮ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ በቀን ወደ ሁለት ጊዜ ማሳደጉን አስታወቀ፡፡

በተከታታይም የመንገደኛ ፍላጎት ቁጥርን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቀን የሚያደርገውን የበረራ ምልልስ እንደሚጨምር መመላከቱን ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የአየር መንገዱ ደንበኞች ባሉበት ቦታ ሆነው የአገልግሎቱን ድረ-ገፅ በመጎብኘት እንዲሁም በተንቀሳቃሽ ሥልኮቻቸው መተግበሪያውን በመጠቀም  ምዝገባ ማድረግና ትኬት መቁረጥ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

አየር መንገዱ የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ዛሬ ከአዲስ አበባ ወደ መቀሌ ዳግም መደበኛ በረራ መጀመሩ ይታወቃል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.