Fana: At a Speed of Life!

በጋምቤላ 2ኛው ምዕራፍ የስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል ሁለተኛው ምዕራፍ የስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

ሁለተኛውን ምዕራፍ የስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክት ወደ ሥራ ለማስገባት ባለ ድርሻ አካላት በተገኙበት የማስጀመሪያ መርሐ ግብር በጋምቤላ ከተማ ተካሂዷል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኡሞድ ኡጁሉ በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር ÷ ክልሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞችን ተቀብሎ በማስተናገዱ ሳቢያ ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ፣ ማህበራዊና አካባቢያዊ ተፅዕኖ ተዳርጓል ብለዋል።

በመሆኑም በስደተኞቹ ምክንያት የሚደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ ነው ማለታቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በተከናወኑ የልማት ሥራዎችም አበረታች ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን አቶ ኡሞድ አብራርተዋል፡፡

በመጀመሪያው ምዕራፍ የስደተኞች ተፅዕኖ ምላሽ የልማት ፕሮጀክት ከ2009 ጀምሮ ስደተኞች በተጠለሉባቸው ጋምቤላ፣ ዲማ፣ ጎግ እና ኢታንግ ልዩ ወረዳዎች÷ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ተፅዕኖን ለመቀነስ በርካታ የልማት ተግባራት መከናወኑ ተገልጿል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.