Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ከ106 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የምግብ ድጋፍ ወደ ትግራይ ክልል ተልኳል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ ከ106 ሺህ ሜትሪክ ቶን በላይ የምግብ ድጋፍና 1 ሺህ 400 ሜትሪክ ቶን መድኃኒት ለትግራይ ክልል መቅረቡ ተገለጸ፡፡

የሰላም ሚኒስትርና የሰሜን ኢትዮጵያ ሰብዓዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ማስተባበሪያ ኃላፊ ብናልፍ አንዷለም እንደገለጹት÷ በሁሉም ኮሪደሮች÷ በቆቦ፣ ጎንደርና አፋር አብአላ በኩል ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ፍጆታዎች ያለገደብ እየቀረቡ ነው፡፡

ከሰላም ስምምነቱ በኋላ 106 ሺህ 957 ሜትሪክ ቶን የምግብ ድጋፍ ወደ ትግራይ ክልል ተልኮ ድጋፉ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች መዋሉንና አቅርቦቱም በታቀደው ልክ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ከሰብዓዊ የምግብ ድጋፍ በተጨማሪ 1 ሺህ 400 ሜትሪክ ቶን መድኃኒት እንዲሁም 10 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች መቅረባቸውንም ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ ተቋማትን መልሶ በመገንባት ዳግም አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን እና እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው÷ የሽረ አውሮፕላን ጣቢያም በቅርቡ የጥገና ሥራው ተጠናቆ ለመደበኛ አገልግሎት ክፍት እንደሚሆን አመላክተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.