Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅሟን ከማስጠበቅ ባለፈ ለአፍሪካ ጥቅምና ፍላጎት መከበር የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች-አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ ብሄራዊ ጥቅሟን ከማስጠበቅ ባለፈ ለአፍሪካ ጥቅም መከበር የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ እንደምትቀጥል አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ ገለጹ።

በተለያዩ የዓለም ሀገራት ኢትዮጵያን የሚወክሉ አምባሳደሮች ከምንም በላይ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅም ማስጠበቅና ሁለንተናዊ የዲፕሎማሲ አቅሟን ከፍ ማድረግ መሆኑ ይታወቃል።

አምባሳደር ታዬ አፅቀሥላሴ÷ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው መስክ ብሄራዊ ጥቅሟን ከማስጠበቅ ባለፈ ለአፍሪካ ጥቅምና ፍላጎት መከበር የላቀ ሚናዋን እየተወጣች መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ በተለይም የሰሜኑን ጦርነት ተከትሎ ባለፉት ሁለት ዓመታት በብዙ መልኩ ቢፈተንም በበርካታ ጥረቶች ችግሮቹ መታለፋቸውን አስታውስዋል።

በተለይም የሰላም ስምምነቱን ተከትሎ በብዙ መልኩ የዲፕሎማሲው መስክ በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን አምባሳደር ታዬ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የውጭ ዲፕሎማሲ በአብሮነትና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ መሆኑን ጠቅሰው÷ ከብሔራዊ ጥቅም ባሻገር የአፍሪካን ጥቅምና ፍላጎት ማስጠበቅን መሰረት ባደረገ መልኩ የዲፕሎማሲ ጥረቷን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል።

ከብሔራዊ እና የአፍሪካን ጥቅም ከማስጠበቅ ባለፈ ችግሮችን በአፍሪካውያን አቅም የመፍታት መርህ እንዲተገበርም አበክራ ትሰራለች ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በቀጣይም የኢትዮጵያን ውስጣዊ አንድነትና ጥንካሬ በማጎልበት በዲፕሎማሲው መስክም አቅሟን ለማጉላት በጋራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.