Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማስጀመሪያ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን (ስማርት ሲቲ) ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ነው፡፡
 
በመርሐ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች የፌዴራልና የከተማው ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
 
አዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን የምታሟላ እና ለነዋሪዎቿ በሁሉም ረገድ ተስማሚ እንድትሆን የሚያስችል ፕሮጀክቶች ይፋ የሚደረጉበት ሲምፖዝየም መሆኑ ተነግሯል፡፡
 
ፕሮጀክቱ የሀገሪቱ ታላላቅ የቴክኖሎጂ ተቋማት የሚሳተፉበትና አዲስ አበባ ላይ በብዙ መስኮች መሰረታዊ ለውጥ የሚያጣ በመሆኑ ለከተማው ነዋሪ ታላቅ የምስራች ነው መባሉን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.