Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የህክምና ኦክስጂን ማምረቻ ፕላንት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የህክምና ኦክስጂን ማምረቻ ፕላንት ተመርቆ ተከፍቷል፡፡

እንዲሁም የተለያዩ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ያካተተ ልዑክ የገብረ ፃዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና አገልግሎት መስጫ ክፍሎችን ተመልክቷል፡፡

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ሰብለ ታምሩ ፥ ሆስፒታሉ ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች አገልግሎት እየሰጠ ነው ብለዋል።

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ተዘዋውረው በተመለከቷቸው የሆስፒታሉ የስራ እንቅስቃሴዎች የሚበረታቱ መሆኑን በመግለጽ በእጥረት የተገለጹ ችግሮች የሚፈቱበት ሁኔታ እንደሚመቻችም ነው የገለጹት ።

የታርጫ እና የገብረ ጻዲቅ ሻዎ አጠቃላይ ሆስፒታሎች ያሉባቸውን ችግር ለመቅረፍ የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ÷ በክልሉ የሲቲ ስካን መመርመሪያ መሳሪያ አቅርቦት እንዲኖርና የወባ ስርጭትን ለመቆጣጠር የተጀመረው ስራ እንዲጠናከር ጠይቀዋል።

በጤናው ዘርፍ እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ላይ በተካሄደ ውይይት የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የጤና ባለሙያዎችና የሀገር ሽማግሌዎች መሳተፋቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.