Fana: At a Speed of Life!

አሜሪካ ለታይዋን የ200 ሚሊየን ዶላር ጦር መሳሪያ ሽያጭ ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለታይዋን 200 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ ፀረ-ታንክ ሽያጭ ውል አጸድቋል፡፡

ስምምነቱ የታይዋንን ዘርፈ ብዙ የመከላከል አቅም በማጎልበት ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተገልጿል፡፡

የሽያጭ ውሉ በታይዋን እና ቻይና መካከል ከፍተኛ ውጥረት እየተፈጠረ በመጣበት ወቅት የተፈጸመ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡

የታይዋን መከላከያ ሚኒስቴር በበኩሉ የተፈጸመው የጦር መሳሪያ የሽያጭ ውል በአንድ ወር ውስጥ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ አስታውቋል፡፡

ለጦር መሳሪያ ሽያጩ አሜሪካን ያመሰገነው ሚኒስቴሩ ይህም ታይዋን ለሚደርስባት ትንኮሳ ፈጣን አጸፋዊ እርምጃ እንድትወስድ ያስችላታል ብሏል፡፡

የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ አሜሪካ ለታይዋን በገፍ የምታከናውነውን የጦር መሳሪያ ሽያጭ ተገቢነት የሌለው ተግባር ሲል ኮንኗል፡፡

ድርጊቱ የታይዋን ማህበረሰብ የጦር መሳሪያ ተሸካሚ ከማድረግ ባለፈ ምንም አይነት ፋይዳ የለውም ማለቱን አር ቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.