የሀገር ውስጥ ዜና

አየር መንገዱ የፊታችን ሰኞ ወደ ሽረ ከተማ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ

By Meseret Awoke

December 29, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰኞ ታህሳስ 24 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሽረ ከተማ በቀን አንድ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡

አየር መንገዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ፥ ወደ መቀሌ የሚያደርገውን መደበኛ በረራ በቀን ወደ ሶስት ከፍ የሚያደርግ መሆኑን ገልጿል፡፡

በተከታታይም የመንገደኛ ፍላጎት ቁጥርን ከግምት ውስጥ በማስገባት በቀን የሚያደርገውን የበረራ ምልልስ ብዛት እንደሚጨምርም ነው የጠቀሰው።