Fana: At a Speed of Life!

ከሕዳር 12 ቀን ጀምሮ 20 ሺህ በላይ ኢትዮያውያን ከሳዑዲ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሕዳር 12 እስከ ታኅሣሥ 20 ቀን 2015 ዓ.ም  ቀን ድረስ  20 ሺህ በላይ ኢትዮያውያን  ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡

ከተመለሾች ውስጥ  19 ሺህ 689 ወንዶች፣ 2 ሺህ 673 ሴቶች እና 724 ህፃናት እና  ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

በትናንትናው ዕለት በተከናወነ በሳዑዲ ዓረቢያ በችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን የመመለስ ሥራ 421 ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

ዜጎችን የመመለሱ ስራ  ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን ÷ ለተመላሾች በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የመቀላቀል ስራ እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.