ስፓርት

ብራዚል በኳስ ንጉሡ ፔሌ ሕልፈት ምክንያት 3 የሐዘን ቀናት አወጀች

By Alemayehu Geremew

December 30, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳስ ንጉሡ ፔሌ ሕልፈት ምክንያት ብራዚል ሦስት የሐዘን ቀናት አወጀች፡፡

የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ የ82 ዓመቱን የኳስ ንጉሥ ፔሌ ሕልፈት ተከትሎ ሦስት ተከታታይ የሐዘን ቀን አውጀዋል።

ብራዚላውያን በምንጊዜም ኮከባቸው ሕልፈት የተሰማቸውን ሐዘን እየገለጹ ነው።

ፔሌ ከሀገሩ ብራዚል ጋር ሶስት የዓለም ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል።