የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ ከኮሮናቫይረስ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 3 ደረሰ

By Meseret Demissu

April 02, 2020

አዲስ አበባ፣መጋቢት 24፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮሮናቫይረስ ከተያዙት ሰዎች መካከል አንድ ተጨማሪ ሰው ማገገሙን የጤና ሚኒስቴር ገለጸ።

ከዚህ ቀደም ከህመሙ ማገገማቸው ከተገለጸው ሁለት ህሙማን በተጨማሪ ሌላ ሶስተኛ ሰው ማገገሙን ዶክተር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።

ከዚም ባለፈ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 65 የላቦራቶሪ ናሙና ምርመራ ተካሂዶ ሁሉም ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው ተገልጿል።

በለይቶ ማቆያ ማዕከል ውስጥ 25 የኮሮናቫይረስ ታማሚዎች መኖራቸውን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገልጸዋል።

ሚኒስትሯ  አንድ ታማሚ በጽኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ እንደሚገኝ  መጠቆማቸውን  ኢ.ዜ.አ ዘግቧል፡፡