የሀገር ውስጥ ዜና

በደብረ ብርሃን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል  አንዲት እናት አራት ልጆችን ተገላገለች

By Mikias Ayele

December 30, 2022

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደብረብርሃን ኮምፕሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አንዲት እናት አራት ልጆችን ተገላገለች።

በሆስፒታሉ የማህፀንና ፅንስ ሀኪም ዶክተር ዳግም ሽመላሽ ÷ ወይዘሮ አፀደ ገብረሀና የተባለችው እናት በተደረገላት የህክምና እገዛ በቀዶ ጥገና አራት ልጆች መገላገሏን ገልፀዋል፡፡

እናትየውንና አራቱም ልጆቿ  በአሁኑ ሰዓት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙም አስረደተዋል፡፡

በሆስፒታሉ ታሪክ አንዲት እናት አራት ልጆችን ስትገላል ይህ የመጀመሪያው መሆኑንም ጠቁመዋል።

ልጆቹ ሁለት ሴትና ሁለት ወንድ መሆናቸውን የገለፁት ዶክተሩ  ከሶስት ቀናት በኋላም ከሆስፒታል መውጣት የሚችሉ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በኤልያስ ሹምዬ