ለአፋር ክልል 500 የውኃ መሳቢያ ፓምፖችና 30 ትራክተሮች ድጋፍ ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ለአፋር ክልል 500 የውኃ መሳቢያ ፓምፖች እና 30 ትራክተሮችን ድጋፍ አደረገ፡፡
ድጋፉን የውሃና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ ለአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ አስረክበዋል።
ኢንጂነር አይሻ በድጋፍ ርክክቡ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ድጋፉ የክልሉን ወጣቶች ወደስራ ለማስገባት እየተደረገ ባለው ጥረት ትልቅ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡
አቶ አወል አርባ ድጋፉ በክልሉ በውሃ እጥረትና በጎርፍ የሚጠቁ አካባቢዎችን በማልማት ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ እገዛ እንደሚደርግ ተናግረዋል፡፡
በሚኒስቴሩ የመስኖ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ብርሃኑ ሌንጂሶ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
በክልሉ ከመካከለኛው አዋሽ ጀምሮ ያሉና ከ120ሺህ ሔክታር በላይ የማልማት አቅም ያላቸውንና ስራ ያልጀመሩ የመስኖ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ወደስራ ለማስገባት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!