Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የ11 ቢሊየን ዶላር የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክት ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና የ11 ቢሊየን ዶላር ታዳሽ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ይፋ አደረገች፡፡

በቻይና ሞንጎሊያ በረሃ ላይ የሚተገበረው ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ በተወዳዳሪነቱ በዓለም ትልቁ እንደሚሆንና 16 ሚሊየን ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ከፀሐይ እና ነፋስ እንደሚያመነጭ አር ቲ ዘግቧል፡፡

ፕሮጀክቱ ቻይና “ከካርበን ልቀት ነጻ የኃይል አማራጭ መጠቀም” በሚል በተመዱ ጉባዔ ላይ ያቀረበችው አጀንዳ አተገባበር ማሳያ መሆኑም ነው የተመለከተው፡፡

የፀሐይ ፣ ንፋስ እና የዓየር ብክለት መጠኑ እንዲቀንስ የተሻሻለ የድንጋይ ከሠል ኃይል በጥምረት በመጠቀምም በዓመት እስከ 40 ቢሊየን ኪሎ ዋት በሠዓት ለማመንጨት እና ዋና ከተማዋን ቤጂንግ ፣ ቲያንጅ የተሰኘችውን የሀገሪቱን ግዛት እንዲሁም ሂቤይን በኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ ለማድረግ ይሠራል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ቻይና ውስጥ በሚገኘው ኩቡኪ በረሃ ታዳሽ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ እንደሚገኝ አር ቲ የቻይናን የዜና ምንጮች ዋቢ አድርጎ ዘግቧል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ኩቡኪ በረሃ ላይ 196 ሺህ የፀሐይ ኃይል መሰብሰቢያ ፓኔሎች 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ኪሎ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል በሠዓት እያመነጩ መሆኑንም ዘገባው ያመላክታል።

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.