Fana: At a Speed of Life!

ከ166 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን 166 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዙ አስታወቁ።

የኮንትሮባንድ እቃዎቹ ከታኅሣሥስ 14 እስከ ታኅሣሥ 20 ቀን 2015 ዓ.ም በተደረገ ክክትል መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል።

ከዚህ ውስጥ 95 ነጥብ 5 ሚሊየን የገቢ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች እና 70 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ የወጪ የኮንትሮባንድ እቃዎች መሆናቸውን ነው የገለጸው።

ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድኃኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የመዋቢያ ዕቃዎች የጦር መሣሪያዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እፆች፣ የምግብ ዘይት እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች እንደሚገኙበት ኮሚሽኑ ገልጿል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.