Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮ ሳይበር ታለንት ልማት ማዕከል ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው የኢትዮ ሳይበር ታለንት የሰመር ካምፕ ፕሮግራም ሰልጣኞች ምርቃት እየተካሄደ ነው።

የምርቃት ፕሮግራሙ በሳይንስ ሙዚየም ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ተመራቂዎቹ በነሐሴ ወር 2014 ዓ.ም አገልግሎቱ ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ ጋር የሰመር ካምፕ በመቅረጽ ሲያሰለጥናቸው የቆዩ ናቸው።

በዛሬው እለትም በታለንት ልማት ማዕከሉ ሲሰለጥኑ የቆዩ 62 ወጣቶች ናቸው የሚመረቁት።

በምረቃ ሥነ ስርአቱ ላይ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እና የታለንት ማዕከሉ አጋሮች ተገኝተዋል።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሳይበር ታለንት ልማት ማዕከል በማቋቋም ባለ ልዩ ተሰጥኦ ታዳጊዎችና ወጣቶችን በመመልመል በተለያዩ ዘርፎች እንደሚያለማ ይታወቃል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.