የሀገር ውስጥ ዜና

በኦሮሚያ ክልል አምስት ከተሞች ለኢንዱስትሪ ዞን በጥናት ተለዩ

By Melaku Gedif

December 31, 2022

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ለኢንዱስትሪ ዞን ለተለዩ አምስት ከተሞች የማስተር ፕላን ዝግጅት የምክክር መድረክ በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ አምቦ፣ ጭሮ፣ ሰንዳፋ፣ ተፍኪ እና ያቤሎ ለኢንዱስሪ ዞን በጥናቱ የተለዩ ከተሞች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

የአምስቱ የተለዩ ከተሞች ማስተር ፕላን በክልሉ የሚገኘውን ሃብትና የባለሃብቶችን ፍላጎት መሠረት በማድረግ በሁሉም አቅጣጫ የኢንቨስትመንት ሥራዎችን ለማሻሻል ትልቅ ሚና እንዳለው ተጠቁሟል፡፡

በቀጣይም ሌሎች ከተሞች በጥናት እንደሚካተቱ መገለጹን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!