Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ በፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገለጹ

አዲስ አበባ ፣ ታኅሣሥ 22 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፖፕ ቤኔዲክት16ኛ ህልፈት የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል።
 
ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷”የካቶሊክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ቤኔዲክት 16ኛ ከዚህ ዓለም በሞት መለየት የተሰማኝን ሃዘን ለካርዲናል ብርሃነ መስቀልና ለመላው የሀገራችን የእምነቱ ተከታዮች እገልጻለሁ” ብለዋል፡፡
 
ፖፕ ቤኔዲክት 16ኛ ዓለማችን የተሻለች እንድትሆን ላደረጉት የዕድሜ ልክ ጥረት ይታወሳሉ ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.