የሀገር ውስጥ ዜና

የምሁራንን ሐሳብ በማካተት ጠንካራ ሀገር መገንባት እንደሚገባ ተገለጸ

By ዮሐንስ ደርበው

January 01, 2023

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር ግንባታ ሂደቱ የምሁራንን ሐሳብ በማካተት የተረጋጋችና ጠንካራ ሀገር መገንባት እንደሚገባ ተገለጸ።

“በሀገር ግንባታ የምሁራን ድርሻ” በሚል መሪ ሐሳብ የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ሀገራዊ ችግር ፈቺና መፍትሔ ጠቋሚ ጉዳዮች ላይ የምሁራን ምክክር እያካሔደ ነው፡፡

የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳኅሉ በመድረኩላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያውያን በሀገር ጉዳይ ላይ የጋራ አጀንዳ ሊኖረን ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

በመሆኑም የተረጋጋችና የሰላም ግንባታ የሚታይባት ሀገር እንዲኖረን ምሁራን በመመካከር መፍትሔ ማምጣት አለባቸው ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!