አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሱሉልታ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 40ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል ሀገር አቋራጭ ውድድር ተጠናቋል፡፡
በማጠናቀቂያ መርሐ ግበሩ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፣የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ፣የምስራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ፕሬዚዳንት ጄነራል ጃክሰን ትዊ እንዲሁም ሌሎች የስፖርት ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡
ከጠዋቱ 2 ሰዓት የጀመረው ውድድሩ በ10 ኪሎ ሜትር የአዋቂ ወንዶች ውድድር በሪሁ አረጋዊ ቀዳሚ በመሆን ሲያሸነፍ ታደሰ ወርቁ እና ጌታነህ ሞላ ተከታትለው በመግባት 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡
በሴቶች ለተሰንበት ጊደይ ትራንስ ኢትዮጵያን ወክላ ስታሸንፍ ጌጤ አለማየሁ ከኦሮሚያ ክልል እንዲሁም መቅደስ አበባ ከአማራ ክልል 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡
በውድድሩ በድብልቅ ሪሌ፣ በ 6 ኪሎ ሜትር ወጣት ሴቶች ምድብ፣ በ8 ኪሎ ሜትር ወጣት ወንዶች ምድብ፣ ከ50 ዓመት በላይ አንጋፋ አትሌቶች እና ከ50 ዓመት በታች አንጋፋ አትሌቶች ምድብ ላሸነፉ አትሌቶች ሽልማት መበርከቱን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!