Fana: At a Speed of Life!

የምሁራን ተሳትፎ በምርምርና ትንተና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዘላቂና አዎንታዊ ሰላም ከመገንባት እንዲሁም ሀገራዊ ምክክሩን ከመደገፍ አንፃር የምሁራን ተሳትፎ በምርምርና ትንተና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ፡፡

“በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና” በሚል ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ካውስል አባላት ምክክር መድረክ ተጠናቋል፡፡

የምክክር ማጠቃለያ መድረኩን የመሩት የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታና የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር አህመዲን መሐመድ እንደገለፁት ፥ የዩኒቨርሲቲ አመራሮች ምሁራኑን የሰው ኃይል ማልማት ብቻ ሳይሆን የዲፕሎማሲ አቅም አድርጎ ከመጠቀም አንጻር ሥራ እንደሚጠበቅባቸው ገልጸዋል።

የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አባል አቶ አሊ ከድር ፥ ዘላቂና አዎንታዊ ሰላም ከመገንባት እንዲሁም ሀገራዊ ምክክሩን ከመደገፍ አንፃር የምሁራን ተሳትፎ በምርምርና ትንተና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።

የወራቤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ቶፊቅ ጀማል የማኅበራዊ ዘርፍ የሚደረጉ ምርምሮች በማኅበረሰቡ ውስጥ የተዛነፉ ጉዳዮች ካሉ በማስተካከልና የመረጃ ምንጭም ሊሆኑበት በሚችልበት ደረጃ ለሀገር ግንባታው የራሳቸውን አስተዋፅኦ ሊያደርጉ እንደሚገባ አንስተዋል።

ከነገ ጀምሮ ለሁለት ቀናት በተመሳሳይ አጀንዳ ላይ የዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ ቴክኒካል ረዳቶችና አስተዳደር ሰራተኞች እንደሚመክሩ ከዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.