ሕጋዊ ዕቃዎችን ሽፋን በማድረግ ተደብቀው የገቡ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ሕጋዊ ዕቃዎችን ሽፋን በማድረግ በኮምፒውተር ሞኒተር ውስጥ ተደብቀው የገቡ 100 ላፕቶፕ ኮምፒውተሮችን ጨምሮ ሌሎች የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎች ተያዙ፡፡
የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የሕግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ስራአስኪያጅ አቶ ፈረጃ አታላይ፥ የዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮችን ሞኒተር ውስጡን ባዶ በማድረግ እና በምትኩ አዳዲስ ላፕቶፖችን፣ ሀርዲስኮች እና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ሌሎች የኤሌክትሮኒከስ ዕቃዎችን በማስገባት እና መልሶ በማሸግ በሕገወጥ መንገድ ሊገቡ ሲሉ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡
በተገኘው የፍተሻ ውጤት መሰረትም በሰነድ ላይ ያልተገለፀው ዕቃ የቀረጥና ታክስ መጠን ከ3 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የተፈፀመው የንግድ ማጭበርበር ተግባር በወንጀል የሚያስጠይቅ በመሆኑ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያለው አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተደረገበት ሲሆን፥ በተያዘው እቃ ላይም የውርስ ውሳኔ የተሰጠበት መሆኑንም ምትክል ስራአስሊያጁ አረጋግጠዋል፡፡
ባለፉት አምስት ወራት ዕቃዎች የጉምሩክ ስነ ስርዓት አጠናቀው ለነፃ ዝውውር ከተለቀቁ በኃላ የአስመጭዎችን የሕግ ተገዥነት ለማረጋገጥ በተደረገ የክትትል እና የቁጥጥር ስራ መንግስት ሊያጣው የነበረ ከ320 ሚሊየን ብር በላይ የቀረጥና ታክስ መጠን ያለው ገንዘብ ማዳን መቻሉን ተናግረዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!