Fana: At a Speed of Life!

አርቲስት  ማሪቱ  ለገሰ ከ22 አመታት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ ወደ ሀገሯ ተመለሰች

አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 24፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)  አርቲስት  ማሪቱ ለገሰ ከ22 ዓመት የአሜሪካ ቆይታ በኃላ በዛሬው እለት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሳለች።

ዝነኛዋ ድምፃዊት ማሪቱ ለገሰ ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ስትደርስ በቤተሰቦቿ፣በሙያ አጋሮቿ እንዲሁም በአድናቂዎቿ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላታል።

ከ6 ሰዓት ጀምሮም በብሄራዊ ቴአትር ለሁሉም ሰው ክፍት በሆነ መድረክ የእንኳን ደህና መጣሽ የኪነጥበብ ዝግጅቶች እየተካሄዱ ይገኛሉ፡፡

የወሎ ዩኒቨርሲቲ ከሰባት ዓመት በፊት ያበረከተላትን የክብር ዶክትሬት ለአርቲስቷ  እንደሚያስረክብም  ታውቋል።

በኢትዮጵያ ቆይታዋ አዲስ አልበሟን ለአድማጭ የምታቀርብ ሲሆን÷ አዲስ አበባን ጨምሮ ደሴ፣ጎንደር እና ባህርዳር ከተሞች የሙዚቃ ሥራዋን ታቀርባለች፡፡

በዚህም የአምባሰሏ ንግስት ማሪቱ ለገሰ ታሕሳስ 29 ቀን 2015 ዓ.ም የመጀመሪያ ኮንሰርቷን በደሴ ከተማ እንደምታቀርብ ታውቋል፡፡

 

በሰላማዊት ተስፋዬ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.